oaa

Mayor's Office on African Affairs
 

DC Agency Top Menu


-A +A
Bookmark and Share

Amharic (አማርኛ)

This page contains information about Office on African Affairs services for Amharic speakers.

Agency Name:

የዲሲ ከንቲባ አፍሪካውያን ጉዳዮች ጽ/ቤት

Mission Statement | ተልዕኮ

የከንቲባ ምዩሪዬል ባዉዘር አፍሪካውያን ጉዳዮች ጽ/ቤት ተልእኮ፣ የሙሉ የጤና፣ የትምህርት፣ የሞያ፣ የንግድ እና ማህበራዊ ጎዳዮችን የተመለከቱ እድሎች ለዲስትሪክቱ የአፍሪካ ማህበረሰብ ተደራሽነቱን ማረጋገጥ ነው። በዲሲ አፍሪካዉያን ማህበረሰብ እና የዲስትሪክቱ መንግስታዊ ኤጀንሲዎች እና ከንቲባ መሃል ሆኖ በማገልገል የአፍሪካ ተወላጅ የሆኑትን የዲሲ ነዎሪዎች እና ልጆቻቸውን የአንዋዋር ጥራት ለማሻሻል ይሻል።

Core Programs/Description of Division | መርሀግብር

አቅም ግንባታ

የአፍሪካውያን ጉዳዮች ጽ/ቤት (OAA) የንግድ እና የበጎ ኣድራጎት ድርጅቶች እድገት ፕሮግራሞቹ አማካኝነት በከተማዋ ለሚገኙ የንግድ ስራዎችን፣ የማህበረሰብ ድረጅቶች እና የሀይማኖት ተቋማትን  ለማሰልጠን የንግድ ድርጅቶች ልማት የምክር አገልግሎት በመስጠት ፤ የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ ፣ተቅዋማትን በመገንባት እና ዘላቂነትን ለማሳደግ የሚያግዙ መረጃዎችን በመስጠት ይሰራል።

  • ንግድ ስራ ልማት - ይህ ፕሮግራም  በዲሲ የሚገኙ የአፍሪካ የንግድ ድርጅቶች የሚያድጉበትን  እና ለከተማ እድገት እና ብልጵግና የሚያበረክቱትን አስተዋጵኦ  እንዲቀጥሉ የሚያስችል መድረክ ያዘጋጃል። የዚህ ፕሮግራም አላማ  የንግድ ድርጅቶችን እርስ በእርስ በማገናኘት ፣የቴክኒክ እና ካፒታል ድጋፍ በመስጠት፣ ለከተማዋ እና ለአለም አቀፍ የንግድ ስራዎች አዳዲስ የስራ እድሎችን በመስጠት የአፍሪካን የንግድ ስራዎች ማጠናከር ነው።
  • የበጎ ኣድራጎት ድርጅቶች ልማት - የማህበረሰብ ድርጅቶች እና የእምነት ተቅዋማት ባህልን ያገናዘበ አገልግሎት እንዲሁም ደህንነቱ የተጠበቀ የመረጃ እና የአምልኮ ስፍራ ለማህበረሰቡ የማቅረብ ልዩ አስተወጵኦ አላቸው።

OAA እነኚህ ለማህበረሰቡ ምሰሶ የሆኑ ድርጅቶች ተገላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች እና ቤተሰቦች የሚሰጡትን አገልግሎት እንዲቀጥሉ የሚያስችላቸው መሳሪያዎች እና ግብአቶች ያሙዋሉላቸው ዘንድ ድጋፍ ያደርጉላቸዋል።

ቅስቀሳ እና ትምህርት

ይህ ፕሮግራም በዲሲ መንግስት  የሚሰጡ አገልግሎቶች እና ፕሮግራሞችን የሚመለከቱ መረጆዎችን ለአፍሪካ ማህበረሰቡ በማድረስ ማህበረሰቡ በአስተዳደሩ ያለውን ተሳትፎ እንዲያሳድግ ያበረታታል። OAA በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ የትምህርት ፕሮግራም በመቅረጵ የማህበረሰቡ አባል በከተማዋ አስተዳደር ስለሚሰጡ አገልግሎቶች፣ አዳዲስ ሀሳቦች ፣ግብአቶች እንዲሁም መረጆዎች እንዲደርሰው ይሰራል። በከተማዋ ከንቲባ በተመረጡ እንዲሁም የማህበረሰቡን ፍላጎት መሰረት ባደረጉ ዘርፎች ፣በጤና፤ በስራ ሀይል ልማት፣ በማህበረሰብ አገልግሎት እና የአካባቢ ደህንነት ዙሪያ ዝርዝር የትምህርት ያስፈጵማል።

ህብረ-ባህላዊ እውቀት እና እድገት

OAA የዲስትሪክቱን የአፍሪካ ነዋሪዎች ስብጥርነት እውቀና ይሰጣል፤ ያከብራል። የዲስትሪክቱ አፍሪካዊ ነዋሪዎችን የለውን የዳበረ ህብረ- ባህል ለማስተዋወቅ እና እንደ ሀብት እንዲቆጠር በማበረታታት ይሰራል። OAA የአፍሪካውያን ማንነት ላይ የሚያጠነጥን ባሕላዊ ዝግጅቶች ፣ የህበረ-ባህልን ጥቀም የሚያሳዩ ውይይቶችን ይዘጋጃል እንዲሁም የማህበረሰብ እድገቶችን ይደግፋል።

ለኣፍሪካውያን ነዎሪዎች አገልግሎቶች

OAA በዲስትሪክቱ አፍሪካዊ ነዋሪዎች፣ በከንቲባውና የዲስትሪክቱ መንግስት ኤጅንሲዎች መካከል ዋነኛ አገናኝ ሆኖ ያገለግላል። የዲስትሪክቱ ነዋሪዎች ችግሮች እና ጉዳዮች ወይም አስቸኩዋይ አገልግሎት ሲፈልጉ ባህልን እና ቋንቋን ያተኮሩ  ምክር እና መረጃዎች ለማግኘት ወደ  OAA ማምጣት ይችላሉ። OAA ከዲስትሪክቱ መንግስት ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች ጋር የተያያዙ የኣፍሪካውያን ነዎሪዎችን  ጥያቄዎችን በኤጅንሲዎች መካካል በሚደረግ ቅንብር (interagency coordination) በኩል ይፈታል።

የወጣቶች ተሳትፎ

OAA ህዝባዊ  አስተወጵኦ እና ተሳትፎን በማበረታታት፣  አመራርን ለማሳደግ እና ወጣቶች እንደ ዲስትሪክቱ ነዋሪ ልዮ ልምዶቻቸውን፣ ጎዳዮችን እና ችግሮቻቸውን የሚገልጱበትን መድረክ በመፍጠር የአፍሪካውያንን ወጣቶች ድምጵ እና ህብረት በማሳደግ ይተጋላል። 

 

Services | ልዩ አገልግሎቶች 

የዲሲ ቋንቋ መብት

OAA የአፍሪካ ተወላጅ የሆኑ የዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ነዋሪዎች በ1996 የወጣውን የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ላንጉች አክሰስ አክት/ሕግ የሚሰጠውን ሙሉ  እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይተጋል። በ1996 የወጣው ሕግ አላማ የእንግሊዘኛ ቋንቋ መናገር፣ ማንበብ፣ መጳፍ እና/ወይም መረዳት ለሚያቅታቸው ግለሰቦች(NEP) እንዲሁም የተወሰነ የእንግሊዘኛ ችሎታ(LEP) ላላቸው የዲስትሪክቱ መንግስት ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች ሰፊ እድል ለመስጠት ነው። አክቱ ወይም ህጉ 34 የዲሲ መንግስት መስሪያ ቤቶች ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን እንዲያደርጉ ይጠይቃል

  • እንግሊዘኛ ቋንቋ የማይናገሩ LEP እና NEP የዲሲ ነዎሪዎችን በተመለከተ መረጃ መፈለግ
  • ትርጉም አገልግሎት እንግሊዘኛ ቋንቋ ለማይናገሩ ሁሉ ማቅረብ፣ ትርጉም አስፈላጊነት ማጥናት እና ቋንቋ የማይናገሩ LEP እና NEP የዲሲ ነዎሪዎችን ከጠቃሚ መረጃ ጋር ማገናኘት
  • ተጠቃሚ ወይም የታወቁ በLEP እና በNEP ኮንስትቲወንት ህዝብ ስለሚነገሩ ቁዋንቆዎች መረጃ መፈለግ

OAA የዲሲ ቋንቋ መብት ሕግ እቅድና አፈጳጰምን ለማሻሻል እና ለመቆጣጠር በሚያደርገው ጥረት ከሰብአዊ መብት ቢሮ (Office of Human Rights - OHR) ጋር በመተባበር  ከእያንዳንዱ 34 የዲሲ መንግስት መስሪያ ቤቶች እና ቋንቋ መብት አስተባባሪ (Language Access Coordinator) ጋር ይተባበራል፣ ይማከራል።

‘እንቆጠር’ ዘመቻ

በ ‘እንቆጠር’ ዘመቻ አማካኝነት OAA ዴሞግራፊክ መረጃዎችን ከአፍሪካካውያን በቀል ንግዶች፣ ድርጅቶች እና ነዋሪዎች ቅጽ በማስሞላት ይሰበስባል። ይህ ጥናት  OAA በቀጣይነት በሚነሱ ጉዳዮች እና የማህበረሰቡ ፍላጎቶችን በተመለከተ ተከታታይ  ፍላጎት መመርመሪያ (needs assessment) ለማካሄድ ዋንኛ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል። የሴንሰስ መረጃ (Census data)  ስለ አፍሪካ ስደተኞች ዝርዝር መረጃ (disaggregated data) ስለማይሰጥ ‘እንቆጠር’ ዘመቻ የሚሰበስበው መረጃ፤ OAA እና የዲሲ መንግስት መስሪያ ቤቶች ስለ ዲሲ ኣፍሪካውያን የበለጠ እንዲያውቁ ይረዳቸዋል። ቅጱ በእንግሊዘኛ፣ በፈረንሳይኛ እና በአማርኛ ይገኛል።

Interpretation Services:  

Contact Info:  

አፍሪካውያን ጉዳዮች ጽ/ቤት
የዲሲ ከንቲባ ምዩሪዬል ባዉዘር ቢሮ
2000 14th Street, NW, Suite 400 North
Washington, DC 20009
(202) 727-5634
www.oaa.dc.gov
[email protected]